“ከቃል እስከ ባህል”

የብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ባሳለፋቸው ውሳኔዎች እና ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላት እና ደጋፊዎች ሚና ላይ የሚመክር መድረክ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ይገኛል።

የብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች እና ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ከመፈጸምና ከማስፈጸም አኳያ የወጣቶች ሚና የላቀ መሆኑም ከመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩም የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የዋና ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ገዛከኝ አንዳርጌ፣ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ደረጄ ጸጋዬ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *