ሮሃ ቡድን የድሬዳዋ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ሻንፒዮን ሆነ

በድሬዳዋ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የድሬዳዋ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች ውድድር በሮሃ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሮሃ ገበያ ከ አዲጋላ ጋር ለዋንጫ የተጫወተ ሲሆን በሮሃ ቡድን 5-2 አሸናፊነት ነው ጨዋታው የተጠናቀቀው።

በመጀመሪያው አጋማሽ የአዲጋላ ቡድን ሁለት ጎሎችን በማስገባት ቀዳሚ ሆኖ ጨዋታውን እየመራ ቢቆይም የሮሃ ቡድን ባስቆጠረው አንድ ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ ጨዋታ 2-1 በሆነ ውጤት ተጠናቆ፤ ከእረፍት መልስ በሁለተኛው አጋማሽ የሮሃ ቡድን በተከታታይ ባስቆጠራቸው አራት ግቦች 5-2 በሆነ ውጤት ሮሃ ቡድን የዲቪዚዮኑ ሻንፒዮን በመሆን ወደ ከፍተኛ ዲቪዚዮን መዘዋወሩን አረጋግጧል።

ጨዋታውን የተከታተሉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በተለያዩ ዘርፎች ላሸነፉ ተጫዋቾች እና ቡድኖች ሽልማት አበርክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *