የድሬዳዋ አሜሪካን ኮርነር በተለያዩ የኮዲን የቴክኖሎጂ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶችን ያስመረቀ ሲሆን በበጎ ፈቃድ ለሚያገለግሉ ግለሰቦች እውቅና ሰቷል።
በአስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤትና በድሬዳዋ አሜሪካን ኮርነር በተዘጋጀው የበጎ ፈቃደኞች የእውቅና እና በማእከሉ በበጎ ፈቃደኞች የተሰረ ፕሮጀክቶችን የማስተዋወቂያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የድሬደዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንዶሰን አባይ መንግስት በሁሉም ዘርፎች ላይ ለዜጎች የሚያስፈልጉ አገልግሎቶችን ለማቅረብ በርካታ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ አሁን ላይም በዚህ እረገድ አንፃራዊ የሆነ መልካም ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ይሁን እንጂ ካለው ውስን አቅም አንፃር መንግስት በሁሉም ዘርፍ ተደራሽ ለመሆን እንደማይችል በመሆኑም ባለድርሻ አካላት ያለውን ክፍተት ከመሙላት አኳያ የሚኖራቸው ሚና የጎላ እንደሆነ ፅህፈት ቤት ኃላፊው ገልፀዋል።
የድሬዳዋ አሜሪካን ኮርነር በተለይ ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ብሎም የቴክኖሎጂ ውጤቶች በማፍለቅ እረገድ የሚሰጠው አገልግሎት ለአስተዳደሩ ትልቅና ወሳኝ አቅም መሆን የሚችል መሆኑን ገልወዋል።
አስተዳደሩ ከዚህ ቀደምም ከማእከሉ ጋር በሚቻለው መጠን በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ወደፊትም በማንኛውም መልኩ የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን አቶ ወንደሰን አረጋግጠዋል።
ማዕከሉ አገልግሎቱን የሚያቀርበው በነፃ ሲሆን ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በውስጡ የያዘ መሆኑን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረጉ አገልግሎቶችን በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ የድሬዳዋ አሜሪካን ኮርነር ፕሮግራም ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘቢባ ሙሰማ በወቅቱ ገልጸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ማእከሉ በአስተዳደሩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚደግፉ ስራዎችን ለማከናወን እቅድ እነዳለው በተለይም ድሬዳዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ፕሮግራም ዳይሬክተሯ ጨምረው ገልፀዋል።
ኮርነሩ የተለያዩ ወጣቶችን የቴክኖሎጂና ዲጂታል ይዘት ባላቸው ዘርፎች ለአመታት እያሰለጠነ እንደሚገኝ፣ ከዚህም በተጨማሪ ከተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች የሚመጡ ተማሪዎችን የኢንተረን ሺፕ እንዲሰሩ እድሎች መፍጠሩን፣ በኮርነሩ የሰለጠኑ ተማሪዎች በተለያዩ አገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ፕሮግራም ዳይሬክተሯ አብራርተዋል።
ምንም እንኳን ማእከሉ ለወጣቱ እንዲሁም ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ በእውቀት በቴክኖሎጂ ልማትና መረጃ ማበልፀግ እረገድ አገልግሎቶችን በበጎ ፈቃድ በነፃ ቢሰጥም ተጠቃሚዎችን በማብዛት በኩል ውስንነቶች እንዳሉ ፣ ይህንንም ለመቅረፍ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ወላጆች፣ማህበረሰቡ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት አንደሚገባ ወ/ሮ ዘቢባ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል የድሬዳዋ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ፅ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ አንድነት ኪዳነ በዚህ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዘመን ተወዳደሪ ሆኖ መገኝት ጊዜው የሚጠይቀው ወሳይ ጉዳይ መሆኑን ገልፀው አስተዳደሩ የተቋማትን አገልግሎትን ጨምሮ በርካታ ዘርፎችን በቴክኖሎጂ የማዘምን ስራዎችን እያከናወነ እንደመገኝ ወደፊትም ይህንን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ዜጎች በተለይ ወጣቶች በመንግስትም ሆነ በባለኡ ድርሻ አካላት የሚቀርቡ እራስን ለማብቃት የሚያስችሉ እድሎቸን በሚገባ መጠቀም እነደሚገባቸው ጠቁመዋል።
የድሬዳዋ አሜሪካን ኮርነር በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚንቀሳቀሱ 6 ማእከላት አንዱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።


