የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር እና ከተረጅነት ለመላቀቅ የተያዙ ግቦች እንዲፈጸሙ የባለድርሻ ተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።
የብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ዛሬም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ነው።
በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፥ ከተረጂነት መላቀቅ የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም ተፈፃሚነት በተቀናጀ አግባብ መሥራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአፈፃፀም ደረጃ እንደ አገር ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቁመው፤ ከቦታ ቦታ ያለውን የአፈጻጸም ልዩነነት ለማጥበብ መሥራት እንደሚገባ አመልክተዋል።
በዘርፉ ውጤታማነትን ለማሳደግ በጋራ ማቀድ እና አፈጻጸሞችን በጥልቀት እየገመገሙ መሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል።


