ህገ ወጥና መርህ አልባ ግብይትን በመቆጣጠር የዋጋ ንረትን ማረጋጋት እንደሚገባ የድሬዳዋ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ገለጹ።

በንግድ ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ለመከታተልእና ድጋፍ ለማድረግ የሚበጅ የቁጥጥር ስርዓት በቢሮው መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በአገራችን ባለፉት አመታት ፈጣን ልማትና መልካም አሰተዳደር ስርአት ለመገንባት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ፕሮግራሞች በመቅረፅ የማሻሻያ ስራዎች መሰራታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፥የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሀርቢ ቡህ ገልፀዋል።

የንግድ አሰራር ስርአቱ አሁን ያለበት ሁኔታ ሲታይ አንዳንድ በንግድ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት የኪራይ ስብሳቢነት አመለካከት ተግባር የተንሰራፋበት የንግድ ስርአት በመከተላቸው ኋላ ቀርነትና ህገወጥ ንግድ ጐልቶ የታየበት እንዲሁም የዘርፉን እድገት የሚመጥን አደረጃጀትና የአሰራር ስርአት ያልዘተረጋለት በመሆኑ ከእያንዳንዱ ዘርፍ የሚፈለገውን ምርትና አቅርቦት ለማመጣጠን አልተቻለም ነው ያሉት።

ይህን ስር የሰደደ ችግር በተጨባጭ ለመቅረፍ ህጋዊና ፍትሃዊ የንግድ ስርአትን በመዘርጋት የአስተዳደሩ የንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እየሰራ መሆኑን ገልጸው የዋጋ ንረትና የአቅርቦት እጥረት እንዳይከስት ከወረዳ ንግድ አመራሮች ጋር የመቶ ቀናት የሥራ አፈፃፀም መከታተያ ስርዓትና ቅፅ በማዘጋጀት ወደ ተግባር የሚገቡበትን አቅጣጫ አስቀምጧል።

የሥራ አፈፃፀም መከታተያ ቅፁ በድሬዳዋ የሚመረቱ ምርቶችን አይነትና ብዛት እንዲሁም በየገበያ ማዕከላቱ በማቅረብ በበቂ ሁኔታ ለማህበረሰብ በሚደርስበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርጓል።ይህንንም በአግባቡ መቆጣጠር እንደሚገባ ምክትል ከንቲባው አቅጣጫ አስቀምጠው ወደ ተግባር አስገብተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *