የዋጋ ንረትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ
************ መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል። ከዚህም ውስጥ 160 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለደሞዝ ጭማሪ ድጎማ የተደረገ ነው። ለነዳጅም 140 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል። በዚህም የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት ወደ 11 ነጥብ 7 ወርዷል። ይህም ከሪፎርሙ ዘመን ጀምሮ ትንሹ የዋጋ ንረት ሆኖ ተመዝግቧል። በቀጣይም ይህን አሃዝ ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ይሰራል።


