አካባቢን በማፅዳት በትንኝ ንክሻ የሚከሰቱ ወባና ተያያዥ በሽታዎችን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑ ተገለፀ::

በድሬዳዋ የወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በቀጠና ሶስት በመንደር 5 እና 6 መርማርሳ እና ጂቲዜድ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የፅዳት ዘመቻ በማከናወን፤ የቤት ለቤት የወረርሽኝ መከላከያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰቷል።

በዚህም በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የወረዳ 02 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አቤል ምስራቅ ወባና ችኩንጉንያን ጨምሮ ሌሎችም ወረርሽኞችን ለመከላከል አካባቢን ማፅዳትና ቁሻሻን ማቃጠል፣ ያቆሩ ውሃዎችን ማፋሰስና የዉሃ ማቆያ እቃዎችን በአግባቡ በመክደን እንደሚገባ አመላክተዋል።

አቶ አቤል አያይዘውም በዛሬው ዕለት ከፅዳት ዘመቻው በተጨማሪ ለማህበረሰቡ ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች ጋር በጋራ በመሆን የቤት ለቤት ወረርሺኝ የመከላከያ መንገዶች ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

አካባቢን በማፅዳት በትንኝ ንክሻ የሚከሰቱ ወባና ተያያዥ በሽታዎችን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነን መሆኑን አቶ አቤል የገለፁ ሲሆን የፅዳት ዘመቻው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

በፅዳት ዘመቻው የወረዳው አመራሮች የሳቢያን ፖሊስ ጣቢያ አመራርና አባላት፣ የገንደ ተስፋ ንዑስ ጣቢያ አመራር እና አባላት የኢንደስትሪ ጤና ጣቢያ አመራር እና ባለሞያዎች፣ ነዋሪዎች እንዲሁም የሴፍቲኔት የፅዳት ሰራተኞችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *