10ኛው የከተሞች ፎረም ከህዳር 6 ጀምሮ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ይካሄዳል

የዘንድሮው 10ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም “የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት” በሚል መሪ ሀሳብ በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ ይካሄዳል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በሰጡት መግለጫ፤ 10ኛው የከተሞች ፎረም ከአፋር ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር ከህዳር 6 እስከ 10 በሰመራ ሎጊያ ከተማ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላት ብትሆንም በከተሜነት ግን ወደኋላ የቀረች መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ፤ ይህንን ለማሻሻል በከፍተኛ ጥረት ዘርፈ ብዙ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ በሀገሪቱ አሁን ላይ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት አይን ገላጭ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

ከህዳር 6 እስከ ህዳር 10 የሚካሄደው የከተሞች ፎረም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኙ የከተሞች ተወካዮች የጋራ መድረክ የሚፈጥሩበት እና ከተሞች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ እንደሚሆንም አመልክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *