የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ ፀደቀ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ከተለያዩ ሹመቶች በተጨማሪ 3 ረቂቅ አዋጆችን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር መካከል የዘላቂ እና ንፁህ ኢነርጂ ተደራሽነት ለማፋጠን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው፥ ፕሮጀክቱ ሀገራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽፋንን አሁን ካለበት 54 በመቶ ወደ 75 በመቶ ለማድረስ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

በ300 መንደሮች የሚኖሩ 1.1 ሚሊዮን ተጨማሪ ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲገናኙ ይረዳል ብለዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ ልማት ማህበር መካከል ለምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽን እና ቀጣናዊ ውህደት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተፈረመውን ተጨማሪ የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ ኢድሪስ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢንያም ኤሮን ሹመት መርምሮ ማፅደቁን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *