በድሬዳዋ የአካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን EAC ፕሮጀክት እየተደረጉ የሚኙ ድጋፎች የዜጎችን ማህበራዊ የኑሮ ዋስትና እንዲረጋገጥ እያገዘ መሆኑ ተገልጿል።
ለአምስት አመት የሚቆየውና ሁለተኛ አመቱን የያዘው የማህበረሰብ አየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት መቋቋም ፕሮጀክት EAC እስካሁን በምግብ ማብሰል ንግድ ዘርፍ፣በባልትና ውጤቶች ንግድ ፣በሸቀጣሸቀጥ ንግድ፣በእንጀራ መጋገር ንግድ፣በብሎኬት ማምረት እና በተሽከርካሪዎች ማጠብ ስራ ዘርፍ ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ተደርገዋል።
በዛሬው የድጋፍ መርሀ ግብር ላይ የድሬደዋ አስተዳደር የአካባቢ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ስራ አስኪሀጅ አቶ አብዱ መሀመድ ፕሮጀክቱ ሰው ተኮር ስራዎች በመሰራታችው የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ የዜጎች ሂወት በዘላቂነት እንዲሻሻል አስችሏል ብለዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት መቋቋም (EAC) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ በላይነህ ደስታ በበኩላቸው በአጠቃላይ ከፕሮጀክቱ 14ሺህ በላይ የሆኑ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።በዛሬው ዐለትም በቀበሌው ለተለዩ 40 ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
የ09 ወረዳ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀሰን ዑመር ፕሮጀክቱ በቀበሌው የተለያዩ ድጋፎችን ለነዋሪዎች እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በኢኤሲ ፕሮጀክት የአማካኝነት ድጋፍ የተደረገላቸሁ ነዋሪዎች ባገኛቹሁት ድጋፍ መነሻነት የቀጣይ ስራቹሁ ውጤታማ ለመሆን ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ስራ አስፈፃሚው ጥሪ አቅርበዋል።
የድጋፍ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ባገኙት ድጋፍ ተነስተው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ እድል የሚፈጥሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እያሰቡ እንደሆነ ተናግሯል።ሲል የዘገበው የአካባቢ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ነው።


