የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ::

በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ወርቅነህ እና የመረጃ አካላትን የማብቃትና ማፍራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቤል ሞላ የተመራ ቡድን በወረዳ 01፣02፣06፣08፣እና 09 የድጋፍ እና ሱፐርቪዥን ስራው ከናውኗል።

በ2018 ዓ.ም ግማሽ አመት የወረዳ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ለማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ የሙያዊ ድጋፍና ክትትል በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በክትትልና ድጋፉ አቶ ብሩክ ወርቅነህ እንደገለፁት በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ ሁነቶችን በወቅቱና በጥራት ተደራሽ ለማድረግ የወረዳዎች የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረው፤የሚዲያና የኮሚኒኬሽኑን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

​ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት ሲኖር መንግስታዊ አሰራሮች ለህዝብ ግልጽ ይሆናሉ ያሉት ኃላፊው ይህም በከተማ አስተዳደሩና በነዋሪው መካከል ያለውን እምነት በማጠናከር መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አቶ ብሩክ በቀጣይ ከወረዳዎች ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሰራና የወረዳዎችን የኮሚኒኬሽን ዘርፍ በቁሳቁስ ለመደገፍና ለማደራጀት ጥረት እንደሚደረግ አመላክተዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ አካላትን የማብቃትና ማፍራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቤል ሞላ በበኩላቸው ድጋፋዊ ሱፐርቪዥኑ በዋነኝነት የወረዳዎች የኮሚኒኬሽ ዘርፍ ለመደገፍና ወረዳዎች ያሉባቸውን ክፍተት ለመሙላት ያለመ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይ በወረዳዎች የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ባለሞያዎችን በስልጠና የማብቃት እንዲሁም በቁሳቁስ የመደገፍ ተግባራት እንደሚከናወኑ አመላክተዋል።

በወረዳ 03፣04፣05 እና 07 የድጋፍ እና ሱፐርቪዥን ስራው በቀጣይ ቀናቶች እንደሚካሄድ የመረጃ አካላትን የማብቃትና ማፍራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቤል ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *