የአሜሪካ ኤምባሲ ልዑክ እና የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ተወያዩ::

የአሜሪካ ኤምባሲ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ጽሕፈት ቤት ልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ከተማ በመገኘት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት አሰጣጥን ለማሻሻል ያለመ ውይይት ከአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ጋር ውይይት አካሄደ።

በምስራቅ አፍሪካ የቀጣናው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኃላፊ የሆኑት ሚስተር ጆርጅ ኤም ቺነሪ የተመራው የልዑካን ቡድን ከቢሮው ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በስፋት ተወያይቷል።

በውይይቱ ወቅት በዋናነት ትኩረት የተደረገው የመምህራንን የማስተማር አቅም ማጎልበት እና የተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎት ማሳደግ በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ነው። የሚስተር ጆርጅ ልዑክ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ተደራሽነት እና ጥራት ለማረጋገጥ የአሜሪካ ኤምባሲ ድጋፍ እንደማይለይ ገልጸዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ለማረጋገጥ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሶ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር የሚደረገው ይህ ትብብር ለከተማው የትምህርት ጥራት መሻሻል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አስታውቋል።

በቀጣይም ሁለቱ አካላት የመምህራን ስልጠናዎችን በማመቻቸት፣ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት እንዲሁም የተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክለቦችን በማጠናከር ረገድ በቅንጅት ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *