በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ፍትህ ሚኒስቴር የፍትህ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ የተመራ ልዑክ የድሬደዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ የሶስት ዓመት የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ የገመገመ ሲሆን 2018 ዓ.ም የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ የመጀመሪያ ግማሽ አመት የስራ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በአስተዳደሩ
በተለይ ባለፉት ሶስት አመት የፍትህ ዘርፉን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።
በዘርፉ ማህበረሰቡን የፍትህ ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም ሰላሟና ፀጥታዋ የተጠበቀ ድሬዳዋን ለማስቀጠል ማህበረሰቡና ሁሉም የፀጥታ አካላት በቅንጅት በተሰራ ስራ አንፃራዊ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ክቡር ከንቲባው ጠቁመዋል።
በቀጣይም የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን በማስቀጠል ብሎም መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በዘርፉ የበለጠ ውጤት እንዲመዘገብ ይሰራል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በአስተዳደሩ ከለውጡ ማግስት ቀደም ሲል የነበሩ የማህበረሰቡን የፍትህ እጦት ለመቅረፍ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን የድሬደዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላማ መሀመድ አብራርተዋል።
በዘርፉ የአገልጋይነት ስሜት በመስራት የህዝብን እሴትና ባህል መሰረት በማድረግ የተሰሩ ስራዎችን የህግ የበላይነትን በማስፈን አኳያ በፍትህ ስርዓትና ወንጀል መከላከል ላይ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አቶ አብዱሰላም ጨምረው ገልፀዋል።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ፍትህ ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ በድሬዳዋ
በፍትህ ዘርፍ በርካታ ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ አፈፃፀሞች መኖራቸውን አውስተዋል።
የህግ የበላይነትን በማስከበር፣የማህበረሰቡንና የአስተዳደሩን ሰላም በማስጠበቅ እንዲሁም በትራንስፖርት እረገድ የለሊት ታክሲ ስምሪት በተቀናጀ መልኩ በመምራት ለወንጀል መከላከል ትልቅ ሚና እንዲኖረው በማድረግ እረገድ የተከናወኑ ስራዎች እንደ ምርጥ ተሞክሮ የሚወሰዱ መሆናቸወን ሚኒስትር ድኤታው ጠቁመዋል።
እነዚህ በተሞክሮ የሚጠቀሱ ስራዎች የተመዘገቡት ከአመራር ጥንካሬና ቁርጠኝነት የመነጨ መሆኑንም ገልፀዋል።
ሉኡካን ቡድኑ ከስደት ተመላሾች ማቆያ መአከል የመስክ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም የፌደራል ፍትህ ሚንስቴር ፣ ድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮና የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት የስደት ተመላሾች መረጃን በመሰብሰብ ቅንጅታዊ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በመድረኩ በተደረገ ውይይት ተገልጿል።


