አስተዳደሩ 7ኛው ብሄራዊ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ፣ፍትሀዊ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አስታወቀ።
የለወጡ መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በፓለቲካው መስክ ካከናወናቸው የለውጥ ስራዎች ውስጥ ታሰረው የነበሩ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ከእስር መፍታትን ጨምሮ አሳታፊ የፓለቲካ ምህዳር የሚፈጠሩ ህጎችን አፅድቋል።
የአስተዳደሩ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር መንግስት የተፎካካሪ ፓርቲዎች በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ አወንታዊ ሚና እንዲኖራቸው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከጋራ ምክር ቤቱ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው “ለአስተዳደሩ እድገት እና ሰላም አብረን በመስራት ሀላፊነታችንን እንወጣለን” በማለት ተናግረዋል።
መጪው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሀዊ እና ሰለማዊ ሆኖ እንዳጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የገለፁት ከንቲባው የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እና አባለት በመስመር ብንለያይም የምንሰራው ለአንድ ሀገር መሆኑን አውቀን በጋራ ለሀገር መስራት ይገባናል ብለዋል።
የድሬዳዋ አሰተዳደር ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዮናስ በትሩ በበኩላቸው ተቋሙ በከተማዋ የፓለቲካ ተሳትፎ እንዲጎለብት የተለያዩ ስራዎችን እያከነወነ እንደሚገኝ ገልፀው መጪው ሀገራዊ ምርጫ የተሳካ እና ውጤታማ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ተናገረዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ አባላት የሆኑ የፓለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች በበኩላቸው ለውጡን ተከትሎ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማት ላይ የተሰራው ሪፎርም አሳታፊ የፓለቲካ ምህዳር መፍጠሩን ገልፀው አስተዳደሩ የሚያደረግላቸው ድጋፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያሰጣቸውን ስራ እንዲከናውኑ አስችሎናል ብለዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ አባል የሆኑ 8 ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች በከተማዋ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ነቁ የፓለቲካ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ደግፈዋል በማለት ለከንቲባ ከድር ጁሀር እና ለብልፅግና ፓርቲ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ፀ/ቤት ኃላፊ ለአቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ምሰጋና እና ሸልማት አበርክተዋል።


