የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታውን አካሄደ።

ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው እለት በአስተዳደሩ ስር ያሉ ሶስት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተገንብተው ለነዋሪው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤት ኮንዶሚኒየም ላይ የመስክ ምልከታውን ያደረገ ሲሆን በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ላይ ያሉትን ማህበራቶች የስራ እንቅስቃሴያቸውን ተመልክተዋል።

የዛሬ የመስክ ምልከታቸውን አስመልክተው አስተያየታቸውን የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ቤዛ ዳምጠው ማህበራቶች በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተደራጅተው አካባቢያቸውን ፅዱ ለኑሮ የሚመች አረንጓዴ ማድረግና ማስዋብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አሁን ላይ በጋራ መኖሪያ ቤት ኮንዶሚኒየም ላይ ሁሉንም የፅዳትና መሰል ስራዎች ለመንግስት የመተው ክፍተቶች መኖራቸውን የተመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉም ሀላፊነት ወስደው ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ግቢያቸውን ማስዋብ እንዲሁም የህብረተሠቡን ጤንነት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ አውጥቶባቸው የተገነቡት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሰው ከገባባቸው በኋላ በቸልተኝነት የሚታዩ ሲሆን በደረቅ ቆሻሻና ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ትኩረት ሰተው ሊሰሩ እንደሚገባና በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ላይ ያሉ ኮሚቴዎች ከማህበራቶች ጋር በመቀናጀት አካባቢያቸውን ፅዱ የማድረግ ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል።

በጋራ መኖሪያ ቤት ኮንዶሚኒየም ሕግ በሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሰራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው ያሳሰበ ሲሆን አሁን ላይ የተመለከቷቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መስተካከል እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ቤዛ ዳምጠው በመስክ ምልከታቸው በጋራ መኖሪያ ቤት ኮንዶሚኒየም ላይ በነዋሪው የተነሱ ጥያቄዎችን በመያዝ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ገልፀው ቋሚ ኮሚቴው ክትትልና ቁጥጥሩን ቀጣይነት ባለው መልኩ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *