በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮና ላስት ማይዝ ግብረሰናይ ድርጅት በጋራ በመሆን በአስተዳደሩ በሙዲ አነኖ የገጠር ክላስተር ለገጠሩ ማህበረሰብ የቅርብ አይታ ችግር ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችና የእይታ ምርመራ፣ልየታና የመነፅር እደላ ዘመቻ ተጀምሯል ።
ፕሬስ ቢዮፒያ ከእድሜ ጋር የተያያዘ የአይን የእይታ ችግር ሲሆን ብዙውን ጊዜ ከ40 አመት እድሜ በኋላ የሚከሰት ችግር ነው።
ይህንን የአይን ችግር በገጠሩ ማህበረሰብ እናቶች ጥራጥሬ ለመልቀም የመርፌ ቀዳዳ ለማስገባት እንዲሁም አባቶች ረዘም ያለ ጊዜ ንባብ ለማንበብ እንዳይቸገሩ በቅርብ እይታ የእለት ተእለት ስራቸውን እንዲያግዛቸው የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ከላስት ማይዝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለማህበረሰቡ በነፃ ልየታና የመነፅር እደላ ዘመቻ መካሄዱ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የሀላፊ ተወካይ አቶ አብዶ ሙሜ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል።
የላስት ማይዝ ሄልስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር እፀገነት አረጋ በበኩላቸው እንደገለፁት
የአይን እይታና የቅርብ እይታ ችግር ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ በሀገሪቱ 10 በላይ ክልሎች የገጠሩ ማህበረሰብን ማዕከል ያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው 72 ሺህ ያህል መነፅሮችን በነፃ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ገልፀዋል።
ዶ/ር እፀገነት አክለውም ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በጋራ በመሆን በአስተዳደሩ ወረዳዎች ከ25 ሺህ በላይ መነፅሮች እንዲሁም በጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች አማካኝነት ልየታ እንደሚከናወን ገልጸዋል ።
የቀለዓድ ጤና ጣቢያ ሀላፊ ሲስተር ደገን ኢሴ በበኩላቸው ለማህበረሰቡ ለተደረገው ድጋፍጨበማህበረሰቡ ስም አመስግነዋል።
በተዘጋጀው መርሃግብር ላይም የአይን እየታ ችግርና በመነፅር አጠቃቀም ዙሪያ
ማብራሪያ ለማህበረሰቡ ተሰጥቶታል ።
ማህበረሰቡ በተደረገለት ልየታና የመነፅር እደላ ድጋፍ አመስግኗል ።
በተደረገው ዘመቻ ላይም የቀልአድ ገጠር ክላስተር ዋና ስራአስፈሚ ፣ሌሎች አመራሮችና የጤና ባለሞያዎች በልየታና በመነፅር እደላ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል ።


