በሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና የስራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥኡመዝጊ በርሄ ለተመራው ቡድን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በዘርፉ እየተከናወኑ ሳላሉ ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከነዚህም መካከል ከስራ እድል ፈጠራ በከተማ እና በገጠር ስለተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁም የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ገለፃ ተደርጓል ።
የልኡካን ቡድኑ በመስክ በመገኘት የድሬዳዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና እና ክህሎት አሰጣጠንና እና በወረዳዎች ሰለሚሰጠው የአንድ ማእክል አገልገሎትን በተመለከተ ምልከታ አድርጓል።


