በአስተዳደሩ የጥምቀት በዓል አከበባር ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ::

የድሬዳዋ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከበባር ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከጸጥታ አካላት፣ ፖሊሰ፣ ከወረዳ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ እና የጸጥታው ምክር ቤት ሰብሳቢ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እንደገለፁት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል እንደሁልጊዜው በሰላም በአብሮነት እና በፍቅር ተከብሮ እንዲያልፍ በኃላፊነት በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የአንድነት፣ የወንድማማችነት/እህትማማችነት እና የሰላም መገለጫ የሆነውን የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ የጋራ ተግባራት ላይ ከምንጊዜውም በላይ በጋራ መስራት እንደሚገባም ነዉ ክቡር ከንቲባ አጽኖት የሰጡት።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ የጸጥታ አካሉ ከአብያተ ቤተክርስቲያን እና ከህብረተሰቡ ጋር በርካታ ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱን ያነስሱት ኃላፊው የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትዕይንቶች የታጀበ በዓል መሆኑ እና በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የአደባባይ በዓል በመሆኑን በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ እንዲያልፍ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅርበት መስራትና አዋኪ የሆኑ ድርጊቶችን በንቃት መከታተል እንደሚገባ አስረድተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በከተማዋ የተከበሩ የአደባባይ በዓላቶችን በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረግ ልምዳቸውን ተጠቅመው ከወዲሁ ዝግጁ መሆናቸው የገለፁ ሲሆን መጪው የጥምቀት በዓልም በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ባለድርሻ አካላት በትኩረት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *