የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ፊት ለፊት የሚገኘውን አደባባይ በኮሪደር ልማት በማስዋብና በማስጌጥ የአካባቢውን ገፅታ ከማሳመር ባለፈ ለወጣቶች የመዝናኛ አማራጭ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ከወጣቶች እንዲሁም ከስፖርቱ ቤተሰብና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በኮምሽኑ ፊት ለፊት የሚገኘውን አደባባይ በመልሶ ማልማት የማስዋብና የማስጌጥ ስራ መሰራቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሀመድ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም አደባባዩ አርጅቶና ፈራርሶ የነበረ መሆኑን ኮምሽነር ካሊድ አስታውሰው አሁን ላይ በመልሶ ማልማት የአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ የአደባባዩን ዙሪያ አጥር

ሁሉሙን የስፖርት አይነቶች በሚወክሉ ቅርፃ ቅርፆች የማስዋብና የማስጌጥ ተግባራት፣የፋውንቴን ስራ፣ ውብ የሆኑና ለአይን የሚማርኩ መብራቶች ተከላን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ የውበት ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል።

አካባቢው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያለበት መሆኑን የጠቀሱት ኮምሽነር ካሊድ አደባባዩ የድሬዳዋን የልማት ግስጋሴ በሚመጥን መልኩ በመሰራቱ ለበርካታ ወጣቶችና ነዋሪዎች የመዝናኛ አማራጭ መሆን መቻሉን ጠቁመዋል።

በፊት ላይ አደባባዩ አርጅቶ ቁሻሻ ይጣልበት የነበረት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀው አሁን ላይ ግን በኮሪደሩ አደባባዩ ተሻሽሎ በአዲስ በመሰራቱ ለአካባቢው ማራኪ ገፅታን ከማላበሱ በተጨማሪ ለወጣቶችም የመዝናኛ ስፋራ እንደሆነ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *