የጥምቀት በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሁኖ ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል ከተለያዩ ደብር የተውጣጡ ወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ::

በዚሁ ከወጣቶች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ መጪው የጥምቀት በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል ፖሊስ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ እንደገባ ገልፀዋል።

ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ ባሻገር በአለም በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኒኮ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል በከተማችን ድሬዳዋ ፍጹም ሰላማዊና የድሬዳዋ መገለጫ በሆነው በመከባበርና በመቀባበል ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የተደራጁ የተለያዩ አደረጃጀት ጋር በትኩረት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ አክለውም ወጣቶች ይህን በመረዳት ለበዓሉ ፍጹም ሰላማዊነት ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር የተከለከሉ ተግባራቶችን ባለመፈጸም እንደከዚህ ቀደም ሁሉ ለሌሎች ክልልና ከተሞች ምሳሌ በሚሆን ደረጃ በዓሉ ማክበር እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ፣ መጋቢ ሰናይት ቀሲስ ኃይለ ማርያም ገብረሚካኤል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ያግዛው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት የሂሳብ ክፍል ሃላፊ መላከ ህይወት ቀሲስ አፈወርቅ አሰፋ የድሬደዋ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮች ከተለያየ ደብረ የተውጣጡ ወጣቶች በተገኙበት በውይይቱ ለተነሱ ሰፊ ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *