የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የከተራ እና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፥ “ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ” ብለዋል።
ከንቲባ ከድር በመልዕክታቸው፥ የጥምቀት በዓል በቅርስነቱ በዩኔስኮ በመመዝገቡ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ እሴት ነው ብለዋል።
የከተራና ጥምቀት በዓል የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ሁነት በመሆኑ፤ በዓሉን ስናከብር የድሬዳዋ እሴት የሆነውን አብሮነት እና ፍቅር በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።
ለአራት ተከታታይ ቀን በዓሉ ሲከበር በሰላም፣ በድምቀትና በክብር እንዲከናወን የምትተጉ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።


