አቶ ብሩክ በመቀጠል እንኳን ለከተራ እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! ከአሉ በኋላ አያይዘው …
በዓለ ጥምቀቱ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ከሃይማኖታዊ ክብረ በዓልነቱ በዘለለ ማኅበራዊ ኑሯችን የሚደምቅበት፣ በልዩ ልዩ አልባሳት የምናጌጥበት፣ ልዩ ልዩ ኅብረ ዜማዎችን የምንሰማበት ባህላዊ እሴቶቻችን የሚስተናገዱበት በዓል ጭምር ነው ብለዋል።
እንደ ጥምቀት ያሉ የአደባባይ በዓሎቻችንን በአማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ ሁላችንም እኩል ልንደክም ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።
መልካም በዓል!!!!!!!


