የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ ያሰባስባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)::

የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ ያሰባስባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ዛሬ ጠዋት በመረቅነው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ይኽን በግልጽ ተመልክተናል ሲሉ አክለዋል።

ሥራው ከአካባቢው በተገኙ የግንባታ ቁሳቁሶች እና በአካባቢ አቅም የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነትን እና ባለቤትነትን ያንፀባርቃልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በባሕል፣ በተፈጥሮ እና ታሪካዊ ጥሪቶች የታደለች በመሆኗ፤ ዛሬ ያለንን ጉልበት እና ጥንካሬ ለመጪዎቹ ተከታታይ ትውልዶች በሚተርፍ መንገድ ሀብቶቿን መግለጥ መቀጠል ይኖርብናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *