ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ::
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት አንድም የመገለጥ፣ ሁለትም የእርቅና ዳግም የመወለድ ምልክት ነው፡፡ በቀደመው ዘመን አዳምና ሔዋን በፈጸሙት ሐጥያት የሰው ልጅ ከአምላኩ ተቀያይሞ የፍዳ ዘመናትን አሳልፏል፡፡ ዳሩ ግን ሰው በሐጥያቱ ልጅነቱን ቢነጠቅም እስከወዲያኛው ጠፍቶ አልቀረም፤ አባቱን ያስከፋ ሥህተት ቢሰራም እስከመጨረሻው ተረግሞ አልኖረም፡፡ አጥቶ የነበረውን የልጅነት ጸጋ በክርስቶስ ዳግም ተቀብሏልና፡፡ ክርስቶስ…


