የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ቋሚ ኮሚቴ አባላት በስራ ተነሳሽነት ክህሎት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አብዲ ሙክታር እንዳሉት በሰው ሀብት ልማት ላይ የአዕምሮ ልማት ወሳኝ ድርሻ ይወስዳል ያሉ ሲሆን የሀገራችንን እድገት ለማፋጠን የአዕምሮ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል::
እንደ ሀገር የጀመርነው የብልፅግና ጉዞን እውን ለማድረግ የአዕምሮ ልማት ላይ በሰፊው እንሰራለን ሲሉም አክለዋል።
ብዙ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብት ባይኖራቸውም የአዕምሮ ልማት ላይ በመስራታቸው ውጤታማ መሆን ችለዋል ያሉት አፈ ጉባኤው እምንሰራቸውን ስራዎች በእውቀት በመስራት ውጤታማነትን እናሳድጋለን ሲሉም አክለዋል።
ከአለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት(IYf) የመጡትና ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ናም ፒል አለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት በኢትዮጵያ በወጣቶች የህይወት ክህሎትና በአዕምሮ ውቅር ላይ በተለያዩ ክልሎች ሲሰራ የቆየ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዕምሮ ስልጠና በጥልቀት የማሰብ ችሎታን ይሰጣል ሲሉም ተናግረዋል።
በስልጠናው ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ቋሚ ኮሚቴ አባላት እየተሳተፉ ይገኛል።
Dire Tv


