የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታር ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታር ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የአፈገሐባኤው ሙሉ መልዕክት የሚከተለው ነው ።

“እንኳን ለ2018 ዓ.ም የጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በአስተዳደሩ ህዝብ የተጣለበትን ሀላፊነት ለመወጣት እና ዲሞክራሲያዊ የህዝብ አስተዳደርን ለማስፈን የሚያስችሉ ህገ-መንግስታዊ አዋጆችን እና ደንቦችን በማውጣት እንዲሁም በምክር ቤቱ የሚወጡ ህጎች በአስፈጻሚ አካላት ያላቸውን ተፈጻሚነት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የአስተዳደሩን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በልዩ ትኩረት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ የሚሰራቸው ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን የማስፈን ስራዎች ያለ ህዝቡ ንቁ ተሳታፊነት ውጤታማ ሊሆኑ ስለማይችሉ የአስተዳደሩ ህዝብ ከምክር ቤቱ ጎን በመሆን የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ በመሆኑ እስካሁን እንደአስተዳደር ያስመዘገብናቸውን የብልጽግና ስኬቶች ማስመዝገብ ችለናል።

በመሆኑም ምክር ቤቱ በማከናወን ላይ ያለውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለማረጋገጥ የአስተዳደሩ ህዝብ በማሳየት ላይ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን እያስተላለፍኩ በአሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ፡፡”

አብዲ ሙክታር

አፈ ጉባኤ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *