“በወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል” – የወረዳ 09 ነዋሪዎች

በድሬዳዋ ወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል ሲሉ የወረዳው ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ አያይዘውም ከኮሪደር ልማቱ በፊት በአካባቢው በስፋት ያረጁ፣ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶች ይገኙ እንደነበረ ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት ግን ያረጁ ቤቶች ውበት ባላው እና በዘመናዊ መልኩ በአዲስ ተሻሽለው እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ለአካባቢ ገፅታ ሳቢ ያልሆኑ ተለጣፊ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶች እየተነሱ መሆናቸውን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ አካባቢው የንግድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የንግድ ቤቶችን ምቹ በሆነ መልኩ የመገንባት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በቀጣይም አካባቢያቸውን የማሳመርና የማልማት ስራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊና የወረዳው ደጋፊ አመራር የሆኑት ኢንጂነር ኡመር ዱአሌ የወረዳው የኮሪደር ልማት በአራት ምዕራፍ ተከፋፍሎ እየተከናወነ እንደሚገኝ የጠቆሙ ሲሆን በዚህም ከአሸዋ እስከ ክርስትያን መቃብር፣ ከባቡራህማ መስኪድ ከፍ ብሎ አስከ ክርስትያን መቃብር፣ ከሀፍካት ድልድይ እስከ ኮተንና ከክርስትያን መቃብር እስከ ታፍ(ከድሬዳዋ ጅቡቲ የሚያገናኘው) መንገድ ድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በህገ-ወጥ መልኩ የእግረኛ መንገድን የዘጉ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶችን የማንሳት ስራዎች መሰራታቸውን ኢንጂነር ኡመር የገለፁ ሲሆን፤በልማቱ የወረዳውን ገፅታ በመቀየር ፅዱና ውብ ለማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር በጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀሰን ኡመር በበኩላቸው እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ 20 ሜትር ራዲየስ የመኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 50 ሜትር ራዲየስ የግልና የመንግስት ተቋማት ዙሪያቸውን እንዲያፀዱ የማድረግ ስራ፣

የዋና ዋና መንገዶች እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በመብራት የማሳመርና የማስጌጥ ተግባራት እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *