የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማና የመውጫ ውይይት አካሄደ።

የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአካል በመገኘት የእቅድ አፈፃፀማቸውን ለመገምገም በተዘጋጀው ቼክ ሊስት እና እየካሄደ ባለው የመስክ ምልከታ የተሰሩ ስራዎችን መነሻ በማድረግ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ ፣ የቢሮ እና የገቢዎች ባለስጣን የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር የበጀት የኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከማኔጅመንት አባላቶቹ ጋር ጥልቅ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጥንካሬና በውስንነት የተነሱ አፈፃፀሞች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የመውጫ የግብረመልስ ውይይት አካሂዷል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እና የገቢዎች ባለስልጣን ግብረመልሶች ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ፣ የገቢ አፈጻጸሙ እየተደረገ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር እና የመጣው ውጤት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እና ባለስልጣኑ የግምገማ መድረክ ላይ የተደረጉ ወይይቶች ግልጽነት ያላቸውና ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገበበት ግማሽ አመትመሆኑና የፕሮጅክቶች አፈፃፀም የዝግጅት ምዕራፍ ስራ፣ በአንድ እቅድ አንድ ሪፓርት በእስትራቴጅክ ግቦች አመርቂ አፈፃፀሞች መመዝገባቸውን ቋሚ ኮሚቴው አንስተዋል፡፡

የመደበኛና የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ የገቢ አሰባሰብና የፋይናንስ አያያዝ የግልፀኝነት ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት፣ ቢሮው የተለያዩ የገቢ አሰባሰብ አማራጮችን በመተግበር የአስተዳደሩን ኢኮኖሚ ለማጠንከር እየሰራ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተዋል፡፡

የአስተዳደሩን ገቢ ለማሳደግ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በጥንካሬ የተገመገመ ሲሆን በውስንነት የተነሱ ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ቢሮው ከሚመለከተው ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት የተገመገመ ሲሆን በውስነት የተለዩትን እንዲታረሙ አቅጣጫ በመስጠት የመውጫ ዉይይታቸውን አጠናቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *