በወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI(world resources institute) የCities for Africa ዳይሬክተር ዶ/ር አክሊሉ ፍቅረስላሴ የተመራ ከደቡብ አፍሪካ ጁሀንስፐርግ፣ ከሩዋንዳ ኪጋሊ እንዲሁም ከኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ሰስተነብል ዲቨሎፕመንት( international institute for Sustainable development) እና ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI ( world resources institute) የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የመንግስት አካላት ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ በሰንካሳ (SUNCASA) በፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎች ላይ የልምድ ልውውጥ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
በዚህም በመድረኩ የተገኙት ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለልኡክ ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ መድረኩ በዋነኝነት እርስ በእርስ መማማሪያና ልምድ መለዋወጫ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሰንካሳ ፕሮጀክት በድሬዳዋ መተግበር ከጀመረ ባጭር ጊዜ ውስጥ በስፋት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረገ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ከንቲባ ከድር ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ በተለይ ለሴቶችና ወጣቶች አረንጓዴ የስራ እድልን እንደፈጠረ ያመላከቱት ከንቲባ ከድር ፕሮጀክቱ የማህበረሰቡን ኑሮ በተጨባጭ ያሻሻለ መሆኑንና ይህም የአካባቢ ጥበቃ እና የኢኮኖሚ ልማት በጋራ ወደፊት እንዲራመዱ ያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
ክቡር ከንቲባ ከድር አያይዘውም በፕሮጀክቱ የተራቆተ መሬት እያገገመ መሆኑን፣ እፅዋቶች እየጨሠሩ መሆኑንና የውሃ ምንጮች መሻሻል እንደጀመሩ ገልፀዋል።
ሰንካሳ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ የአረንጓዴ ሌጋሲ ኢንሼቲቭ ጋር የተናበበ መሆኑን ከንቲባ ከድር አመላክተዋል፤በቀጣይም የድሬዳዋ አስተዳደር የሰንካሳ ፕሮጀክት ስኬትን ለማስፋት ቁርጠኛ መሆኑ ገልፀዋል።


