በመቶ ቀናት እቅድ በተቀመጠው አንድ ግዙፍ ኢንቨስትመንት የመሳብ ግብ መሰረትም መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻን ጨምሮ የተለያዩ ሞዴል የኤሌክትሪክ መኪኖች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት ማስተላለፉንም ቢሮው አስታውቋል።
በቅርቡ ይፋ የሚደረገው መተግበሪያ ተገልጋዩ ወደ ተቋሙ የሚያደርገውን የአካል ምልልስ በማስቀረት ከጊዜ፣ ጉልበትና ሀብት ብክነት ነጻ በማድረግ ባለጉዳይ ባለበት ስፍራ ሆኖ የቢሮውን አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ቱሩፋት መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሳጅድ አሊዪ ገልጸዋል።
መተግበሪያው ተገልጋዩ በራሱ የሚፈልገውን ግልጋሎት የጊዜና የቦታ ወሰን ሳይገድበው ልክ እንደ መብራት፣ ውሃ፣ ቴሌኮሙኒኬሽንና ሌሎችም ዘርፎች ክፍያዎችን መክፈል፤ ለከፈለውም ገንዘብ ኤሌክትሮኒክ የሆነ የደረሰኝ ማረጋገጫ ማግኘት የሚያስችል SELF SERVICE PORTAL ሰርዓት ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ትርጉም ባለው መልኩ የሚቀንስ መሆኑን ነው ኢንጂነር ሳጅድ አሊዪ ያስታወቁት::
መተግበርያው ተሰርቶ የተጠናቀቀ መሆኑንና በመቶ ቀናት ዕቅዱ ውስጥ ቢሮው ይፋ እንደሚያደርገውም የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማናጅመንት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሳጅድ አሊዪ ገልጸዋል ፡፡
ቢሮው በአስተዳደሩ የሚገኙ የመሬትና የቤት መረጃዎች በዲጂታል ቋት በቀላሉ ሙሉ መረጀ ማግኘት የሚያስችል መተግበርያ አሰርቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ኃላፊው ጨምረው አሳውቀዋል ፡፡
ግዙፍ ኢንቨስትመንት የመሳብ ግብ እንደ አስተዳደር ከሌሎች ሴክተሮች የሚጋሩት ቢሆንም መሬት አልምቶ ማዘጋጀት ለኢንቨስትመንት ቀዳሚ በመሆኑ የኤሌክትሪክ የቤት መኪና ጨምሮ የህዝብ ማመላለሻና የጭነት መኪናዎችን መገጣጠም ለሚችል ኢንቨስትመንት መሬት መተላለፉን ኢነጂነር ሳጅድ አሊዪ አስታውቀዋል ፡፡
ቦታውን የተረከበው በAM ቢዝነስና ኢንቨስትመንት ግረፕ AM ሞተርስ በአስተዳደሩ በተሰጠው ቦታ ከዚህ በፊት በአውቶሞተቲቭ ዘርፍ ያከበተውን ልምድና ተሞክሮ በማላቅ እንደሚሰራ የAM ሞተርስ መኪና መገጣጠምያ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ሜደቅሳ ተናግረዋል ፡፡ የ AM ሞተርስ ስራ አስኪያጅ አያይዘውም ከድሬዳዋ ዩነኒቨርሲቲ ጋር በቀርበት በመስራት ተማሪዎች የመመረቅያ ፕሮጀክቶቻቸውን ሲያቀርቡ በቦታው በመገኘት ጭምር የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎታቸውን ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያሟሉ ተናግረዋል ።
የልማት ተነሺዎችን ቅሬታ ተቀብሎ የሚፈታ ግብረ ኃይል አዋቅሮ እያስተናገደ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በተቋሙ የሚገኙ ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ ብሔራዊ መታወቅያ ፋይዳ ያላቸው ሲሆን አገልግሎት ፍለጋ የሚመጡ ደምበኞችም ፋይዳ ይዘው መገኘት እንዳለባቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተረዱ መምጣቸው ተገልጽዋል ፡፡


