አዲስ የተገነባው የአርጆ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ እውነታዎች

• በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዕድገት ውስጥ እንደ አንድ ትልቅ ምዕራፍ የሚጠቀሠው የአርጆ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ ከውጭ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት ለመተካት የሚያግዝ ነው።

• የአርጆ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር በሚገኘው ብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን የሚተዳደር ነው።

• ፋብሪካው ለኢትዮጵያ ዕድገት ወሳኝ ለሆኑት የሲሚንቶ፣ የብረት ብረት እና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች የድንጋይ ከሰል ያቀርባል።

• ፋብሪካው በሰዓት 200 ቶን የማምረት አቅም ያለው ሲሆን 250 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው።

• ኬሚካል አልባ አሰራርን በመከተል ለአካባቢ ደህንነት መረጋገጥ አስተዋጽኦም ያደርጋል።

• አንድ ቢሊዮን ብር የሚሆን ገንዘብ ኢንቨስት የተደረገበት ፋብሪካው በአንድ ዓመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ነው።

• ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኢንዱስትሪ ዕድገትን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር እንዴት አጣምራ መጓዝ እንደምትችል የሚያሳይ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *