ኢትዮጵያ ለድንጋይ ከሰል በየዓመቱ የምታወጣውን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ የምታስቀርበት ፋብሪካ

ኢትዮጵያ ለድንጋይ ከሰል ግዢ በየዓመቱ የምታወጣውን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ የምታስቀርበት ግዙፉ የአርጆ የድንጋይ ከሰል ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀምሯል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ የገጸ ምድር እና የከርሰ ምድር የማዕድን ሀብቷን አልምታ እና እሴት ጨምራ በመጠቀም በኩል ለረጅም ዓመታት በቁዘማ ቆይታለች ብለዋል።

ከለውጡ ወዲህ ግን የማዕድን ዘርፉን ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ በማድረግ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል።

የምርት መጓደል እንዳይኖር በመሠራቱ የሲሚንቶ ገበያ ላይ የምርት መጓደል እንዳይገጥማቸው እና በገበያ ላይ የተረጋጋ የሲሚንቶ አቅርቦት እንዲኖር መሠራቱንም ነው የተናገሩት።

በኢትዮጽያ በዓመት እስከ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን የሚደርሰውን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት ሙሉ በሙሉ መተካቱንም ኢንጂነር ሀብታሙ ገልጸዋል።

ልክ እንደ ድንጋይ ከሰል ፋብሪካው በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት የሴራሚክ ፍላጎታችንን በሀገር ውስጥ የምንተካባቸው ግዙፍ ፋብሪካዎች በቅርቡ ይመረቃሉ ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *