ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአርጆ ዲዴሳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የጎበኙ ሲሆን፤ የደረሰበት ደረጃም አስደናቂ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይኽ ትልቅ ፕሮጀክት በቅርብ ዓመታት ግንባታው ተፋጥኖ ወደ መጠናቀቂያው መቃረቡን ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቱ ለአገልግሎት በሚበቃበት ጊዜም የተለያዩ የአዝርዕት ልማትን በመደገፍ እንደሀገር የተጀመሩ የምግብ ሉዓላዊነት ጥረቶችን የሚያግዝና በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችን በመጥቀም ግብርናውን የሚያሻግር እንደሚሆን ገልጸዋል።
ይኽ ፕሮጀክት ባላሰለሰ ጥረት እና የታቀደለትን ግብ በማሳካት የአካባቢውን ማኅበረሰብ ኑሮ ከፍ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።


