በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) የሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ አቻቸውን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወቃል።
ታዲያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደርሶ መልስ ጨዋታውን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ አቻቸው ጋር በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ለማድረግ ነው ድሬዳዋ ከተማ የገባው።
ልዑኩ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ፣ በካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ጨዋታው የፊታችን ማክሰኞ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።


