በቃላድ ክላስተር የብልጽግና ፓርቲን ወክለው በ7ኛው ዙር ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚተዋወቁበት መርሃ-ግብር ተካሄደ።

ይህ የብልጽግና ፓርቲ በድሬዳዋ አስተዳደር በቀለአድ ክላስተር የ7ኛው ዙር ምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ትውውቅ መድረክ የተዘጋጀው፣ ማህበረሰቡና ተወካዮቹ በደንብ እንዲተዋወቁና እንዲቀራረቡ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ በቃላድ ክላስተር የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ ዕጩዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

የቃላድ ክላስተር ነዋሪዎች ለእጩዎቹ ደማቅ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፣ በምክር ቤት ድምፅ እንዲሆኑ ከብልጽግና ፓርቲ ለቀረቡት ዕጩዎች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *