ዕጩዎችን በመወከል በዋሂል ክላስተር ለተገኙ ታዳሚዎች ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የድሬዳዋ አስተዳደር የካቢኔ አባልና የአስተዳደሩ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነጻ ፣ ገለልተኛ እና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲያቸው ብልጽግና በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙሉካ በዋሂል ክላስተር የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ ተመልምለው የቀረቡ ዕጩዎች ቀደምሲል በምርጫ ቦርድ ከመመዝገባቸው በፊት በተደጋጋሚ ማህበረሰቡ አስተያየት የሰጠባቸውና ግምገማዎችን በማለፍ በክላስተሩ የሚገኙ ወረዳዎችን በመወከል ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 23 እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1 ተወዳዳሪ ዕጩዎችን ከምርጫ ቅስቀሳ በፊት በአካል ተገኝቶ ለማስተዋወቅ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ቃልን በተግባር የሚለውን መርህ በመከተል በስምንት ዓመት ብቻ ላለፉት በርካታ አመታት ያልተሰሩ ስራዎችን በመስራት ያሳየና ኢትዮጵያን ወደ አፍሪካ ተምሳሌት ሀገርነት እያንደረደራት ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል ፡፡
በዕጩዎች ትውውቅ መድረኩ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ጀማል ስሪ የተባሉ የወሂል ወረዳ ነዋሪ እንደተናገሩት ዕጩዎቹን ከዚህ ቀደም እንደሚያውቋቸው ገልጸው ፤ቀደም ሲል በከተሞች ታቅዶ የነበረው የኮሪደር ልማት ውጤታማ በመሆኑ አሁን ደግሞ በገጠር የተጀመሩት የልማት ስራዎች ጎን ለጎን በተጨማሪ በታቀደው የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ከኛ ጋር በመሆን እንደሚያሳኩት ታላቅ እምነት አሳድሮብኛል ብለዋል ፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ለሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ያዘጋጃቸውን ዕጩዎች በሌሎቹም ክላስተሮች በተመሳሳይ ለህዝብ እያስተዋወቀ ይገኛል ፡፡


