የድሬዳዋ አስተዳደርና የሐረሪ ክልል አመራሮችን ያሳተፈና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ደማቅ ስፖርታዊ ውድድር በሐረር ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል

በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተመራ ልዑካን ቡድን ሐረር ከተማ የገባ ሲሆን፣ ለልዑኩ በሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በሁለቱ አጎራባች ከተሞች መካከል ያለውን ታሪካዊ ወንድማማችነትና ማኅበራዊ መስተጋብር ይበልጥ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር፣ የአመራሮች መቀራረብ ለሁለቱ ሕዝቦች አብሮነት ትልቅ ተምሳሌት መሆኑ ተገልጿል።

የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩ መጠናከሩ፣ የፊታችን ግንቦት ወር የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል።

በአሁኑ ሰዓት በሐረር ስታዲየም እየተካሄዱ በሚገኙት የተለያዩ አዝናኝና አጓጊ ስፖርታዊ ውድድሮች መካከል የገመድ ጉተታ አንዱ ሲሆን፤ በድሬዳዋና በሐረሪ ክልል አመራሮች መካከል በተደረገው ውድድር የድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች ተፎካካሪዎቻቸውን አሸንፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *