የድሬዳዋ አስተዳደር ልዑክ በሐረሪ ክልል ያደረገው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና የፖለቲካ ንቅናቄ መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ::
በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሃር የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በሐረሪ ክልል ያደረገውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከሪያ ጉብኝት በስኬት አጠናቋል። ጉብኝቱ በሁለቱ አጎራባች አካባቢዎች መካከል ያለውን ታሪካዊና ማኅበራዊ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ፣ በጋራ የልማትና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሃር በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ “ድሬዳዋና ሐረሪ በጂኦግራፊ ብቻ ሳይሆን በታሪክ፣…


