ከንቲባ ከድር ጁሀር በድሬዳዋና ሐረሪ አመራሮች የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ግብ አስቆጠሩ

በድሬዳዋ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል አመራሮች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ በሐረር ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ታላቅ ስፖርታዊ መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ባሳዩት ልዩ ብቃት ግሩም ግብ ማስቆጠር ችለዋል።

የከንቲባው ግብ የመሪዎችን ንቁ ተሳትፎና የአካል ብቃት ጥንካሬ ከማሳየቱም በላይ፣ በሁለቱ ወንድማማች አመራሮች መካከል ያለውን መቀራረብ ይበልጥ አዝናኝና ደማቅ እንዲሆን አድርጎታል።

ግቡ በሚቆጠርበት ወቅት በስታዲየሙ የተሰማው የደስታ ድምፅ ስፖርት የሰላምና የፍቅር መገለጫ መሆኑን በተጨባጭ ያሳየ ነበር።

በመጀመሪያው አጋማሽ በሐረሪ ክልል 2 ለ 1 ውጤት የቀጠለው ይህ የወዳጅነት ጨዋታ፣ በሁለቱ አካባቢዎች መካከል ያለውን አብሮነትና ወዳጅነት የሚያድስ ስፖርታዊ ክስተት ሆኖ አልፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *