‘በምርጫ ካርዳችን መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል”የወረዳ 07 እና 09 ነዋሪዎች

ወ/ሮ አረጋሽ ተካ በድሬዳዋ አስተዳደር የ07 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በቡና ንግድ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።ምርጫ የነገውን እጣፈንታችንን የምንወስንበት ዲሞክራሲያዊ መብታችንን የምንተገብርበት እንደሆነ አምናለው ይላሉ።

በመሆኑም ነገ በሚደረገው ምርጫ ቀድመው በወሰዱት የምርጫ ካርድ የሚበጀኝን ለመምረጥ ተዘጋጅቻለው ሲሉ ገልጸዋል።

እንደ እሳቸው ሁሉ የ09 ቀበሌ ነዋሪው አቶ አብዱልፈታህ ሼህ አብዱረህማን ቀደም ሲል ሁለት አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ መሳተፋቸውን ገልፀው የዘንድሮው ምርጫ በተለየ መልኩ መነቃቃት እንዳለ መታዘባቸውን ያስረዳሉ።በነገው ምርጫም እንደ ዜጋ ለመምረጥ በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ነግረውናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *