የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ፊት ለፊት የሚገኘውን አደባባይ በኮሪደር ልማት በማስዋብና በማስጌጥ የአካባቢውን ገፅታ ከማሳመር ባለፈ ለወጣቶች የመዝናኛ አማራጭ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ከወጣቶች እንዲሁም ከስፖርቱ ቤተሰብና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በኮምሽኑ ፊት ለፊት የሚገኘውን አደባባይ በመልሶ ማልማት የማስዋብና የማስጌጥ ስራ መሰራቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሀመድ ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም አደባባዩ አርጅቶና ፈራርሶ የነበረ መሆኑን ኮምሽነር ካሊድ አስታውሰው አሁን ላይ በመልሶ ማልማት የአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ የአደባባዩን ዙሪያ አጥር ሁሉሙን…


