በዓመት እስከ 130 ሚሊዮን ተጓዦችን የሚያስተናግድ ኤርፖርት እንገነባለን፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በአፍሪካ ግዙፍ የሚያስብለንን ትልቅ ኤርፖርት ለመገንባት ጥናት አጠናቀናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክርቤት ማብራሪያቸው ወቅት ተናግረዋል። አሁን ያለው የቦሌ ዓለም ዓቀፍ ኤርፖርት በዓመት ከ25 ሚሊዬን ለማይበልጡ መንገደኞችን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ይህን ለማሳደግ አዲስ ኤርፖርት መገንባት ማስፈለጉን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል። በዚህም በዓመት ከ100 እስከ 130 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል አዲስ ኤርፖርት ለመገንባት ጥናቱ…


