ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ለማህበረሰቡ አገልግሎት ሰጪ ንድፈ ሀሳቦችን መስራት መጀመሩን አስታወቀ።
ለማህበረሰቡ አገልግሎት ሰጪ የመጀመሪያ ዙር የንድፈ ሀሳቦች መገምገሚያ ወርክሾፕ በዛሬው እለት በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ተካሄደ፡፡ ዩኒቨርስቲው ካሉት ተልዕኮዎች አንዱ የአካባቢውን ማህበረሰብ ማገልገል ነው ያሉት የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ጉዳዩች ምክትል ፕሪዘዳንትና የፕሪዘዳንቷ ተወካይ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀፍና ችግር ፈቺ ንድፈ ሃሳቦችን ለመስራት የበጀት ችግር እንዳይገጥም በቂ በጀት በመበጀት ወደ ስራ መገባቱን በመግለፅ በዛሬው እለት ከሚቀርቡት…


