በፅዳት ዘመቻውን የተለያዩ እምነት ተከታይ የሆኑ የአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች የቀበሌው አስተዳደርና የፖሊስ አባላት በጋራ በመሆን ነው ያከናወኑት::
ከፊታችን ሰኛ ጥር 10 ቀን ጀምሮ በከተራ የሚጀምረው የጥምቀት በአል በሰላም በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ማስቻልን ታሳቢ አድርጎ በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ ላይ የድ/ዳ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጉሌድ ድርዬና የቀበሌ 09 ዋ/ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀሰን ኢጌ ባስተላለፉት መልእክት “በፅዳት ዘመቻው ለተሳተፉ ወጣቶችና ሌሎች የህ/ብ ክፍሎች እንዲሁም የፖሊስ አባላትን አመስግነው በከተማችን ድሬዳዋ በሀያማኖት መካከል ያለውን የቆየ የመቻቻል የአብሮነትና አንድነት ባህል ሆን ብለው የጥፋት አላማን በማንገብ ለመከፋፈል እና ለማጋጨት የሚጥሩ አካላትን ሴራ በሚገባ በመረዳትና በማምከን መገለጫው የሆነውን አብሮነቱን ይበልጥ አጠናክሮ ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል” ብለዋል ::
በጽዳት ዘመቻው ላይ ያገኘናቸው የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎች ለድሬ ፖሊስ በሰጡት አስተያየት ቀድሞ የምንታወቅበትና መገለጫችን የሆነውን አብሮነትና ወድማማችነት ይበልጥ አጠናክረን በአንድነት የምንጓዝበት ግዜ እንደመሆኑ ይህንኑ ለማረጋገጥ ነው ታቦታቱ የሚያልፉባቸውን መንገዶች ያፀዳነው :: በቀጣይ ቀናትም የበአሉ አክባሪ ከሆኑ ክርስቲያን ወንድሞቻችን ጋር በመሆን በአሉ ሰላማዊ ሆኖ በድምቀት ተከብሮ እንዲያልፍ የሚጠበቅብንን ሁሉ እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል::
የፅዳት ዘመቻው ም/ል ኮሚሽነር ጉሌድ በተገኙበት በአካባቢው የተለያየ እምነት ተከታይ በሆኑ የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎች ፣ የቀበሌው አስተዳደርና የቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ አመራርና አባላት የተከናወነው::
ምንጭ ፡ ድሬ ፖሊስ


