ተረጂነት የመፍጠር አቅም እና የመሥራት ጉልበትን የሚበላ ካንሰር ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ተረጂነት የመፍጠር አቅም እና የመሥራት ጉልበትን የሚበላ ካንሰር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ለምክር ቤቱ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መሥራት እየቻለ ተረጂ የሆነ ሰው በዕድሜ የገፋ ቢሆንም በዚህ ምክንያት ተገቢውን አክብሮት እንደማያገኝ ነው አክለው የተናገሩት። ኢትዮጵያውያን ለክብራችን ስንል ከተረጂነት መላቀቅ አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ፖለቲካ ሳይሆን የኢትዮጵያ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብዝሃ ዘርፍ ትብብርን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል። መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው። ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ…

Read More

የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ

ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም። በሪፎርሙ አመካኝነት ከ4 አስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም መንግስት አንድም ዶላር የንግድ ብድር አልወሰደም። ይህም እዳን ለመቆጣጠር ያለንን ጽኑ አቋም ያሳያል።

Read More

“2017 በኢትዮጵያ ታሪክ እና የታሪክ እጥፋት ውስጥ ትላልቅ ጉዳዮች ያሳካንበት፤ ይቻላሉ ተብለው የማይታሰቡ ጉዳዮች ተችለው ያየንበት፤ የተከናወንበት፤ ቃል የገባንባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች የፈፀምንበት፤ እጅግ የስኬት ዓመት በጋራ ማሳለፍ ስለቻልን እንኳን ደስ አላችሁ!” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Read More

በኢትዮጵያ ታሪክ ታላላቅ እና አይቻሉም የተባሉ ጉዳዮችን እውን ያደረግንበት የስኬት ዓመት ነው ያሳለፍነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ ታላላቅ እና አይቻሉም የተባሉ ጉዳዮችን እውን ያደረግንበት የስኬት ዓመት ነበር ብለዋል። የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የሀገሪቱን ግብርና መር የኢኮኖሚ አካሄድ፤ ከአንድ ዘርፍ ወደ ብዝኃ ዘርፍ በመቀየር ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግብርናን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል። ለአብነትም ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። በምርት ደረጃም ሩዝን ወስደን ብናይ ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትንም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድግነዋል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገቢን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ

**************** ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት ነው። ለአብነትም ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል። በዚህም የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ ኢኮኖሚ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል

*************** በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በማዕድን ዘርፍ ትልቅ እመርታዎች ተመዝግበዋል፣ በዚህ ዓመት ያለጥርጥር ዕድገታችን ባለሁለት አሀዝ ይሆናል፣ 900 ቢሊየን ብር የእዳ ሽግሽግ ተደርጎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሞት ድኗል፣ በ2017 ዓ.ም መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ሳይበደር ኢኮኖሚውን መርቷል፣ የኢኮኖሚ ሪፎርማችን ዓለምአቀፎቹ ተቋማት እውቅና የሰጡት እና ለሌሎችም ሀገራት ልምድ የሚሆን ነው፣ በተኪ ምርቶች በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ድኗል፣…

Read More

የዋጋ ንረትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ

************ መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል። ከዚህም ውስጥ 160 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለደሞዝ ጭማሪ ድጎማ የተደረገ ነው። ለነዳጅም 140 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል። በዚህም የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት ወደ 11 ነጥብ 7 ወርዷል። ይህም ከሪፎርሙ ዘመን ጀምሮ ትንሹ የዋጋ ንረት ሆኖ ተመዝግቧል። በቀጣይም ይህን አሃዝ ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ይሰራል።

Read More

“የኢትዮጵያን ዕድገት ጥሩ አፍንጫ ያለው ሰው ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ በሽታ ያውቀዋል። ጥሩ ዐይን ያለው ሰው በማየት ብቻ ሊገነዘበው ይችላል፤ ጥሩ ጆሮ ያለውም ሰው በማድመጥ ሊረዳው ይችላል፤ የኢትዮጵያ ዕድገት የሚያጠራጥር ጉዳይ ስላልሆነ ወይ ዐይናችሁን፣ አፍንጫችሁን ወይም ጆሯችሁን መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቀው።”

Read More