ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለአዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በተመለከተ ካነሱት

******* አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።

Read More

የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ ይቻላል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

*********************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸው፣ ይህም በኢትዮጵያ…

Read More

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

***************** የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላኖች ከመነሻቸው በቂ ነዳጅ ይዘው ረጅም መንገድ በሚያስጉዛቸው መልኩ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ይህም ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአቬሽን ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት ነው ብለዋል፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያው ሥራ ሲጀመር ማኅበራዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በቂ ዝግጅት ተደርጎበት፣ አርሶ አደሮች ቀድሞ መኖሪያ ቤት ተሠርቶላቸው ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲነሱ መደረጉንም…

Read More

በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የጋዝ ክምችት ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

******* ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕድንና ጋዝን በተመለከተ ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ፤ የማዕድን ሥራችን በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ አንድ ከመቶ ድርሻ እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በተለይም የጋዝ ፕሮጀክት ባስጀመርንበት ሶማሌ ክልል አካባቢ ትልቅ ክምችት መኖሩን አስታውቀው፤ በአንድ ቦታ ብቻ 21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የጋዝ ክምችት ኢትዮጵያ እንዳላት በሶስተኛ ወገን መረጋገጡን ጠቅሰዋል። ይህንንም ሃብት ላለፉት ዓመታት…

Read More

የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሡት ሐሳብ

****************** የኮሪደር ልማት የቦታና ጊዜ ምልከታን የሚቀይር ነው። ለአብነትም በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተገንብቷል። በርካታ ወጣቶች ወደ ስፖርት እየተመለሱ ነው። ይህም ማህበረሰብን የመገንባት ስራ ነው። የትውልድ ስነ ልቦና ስብራትን እያረቀ ያለ ስራም ጭምር ነው። ይህን ማንም ሰው የሚያየው፤ ማንም ሰው የሚናገረው ጉዳይ ነው።

Read More

የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክትን በ24 ወራት ውስጥ አጠናቅቀን እንጨርሳለን

******** ልክ እንደተፈጥሮ ጋዝ ሁሉ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት እንዳለ በሶስተኛ ወገን መረጋገጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ነዳጅ ማጣሪያውንም በ24 ወራት ውስጥ አጠናቅቀን እንጨርሳለን ብለዋል። የጋዝና ነዳጅ ሥራ ከውጭ የሚገባውን ኃይል በመተካት የወጪ ምንዛሬ ለመቆጠብ ይረዳናል ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለነዳጅና ለማዳበሪያ ከፍተኛ ሃብት ታወጣለች፤ ይህን ማስቀረት ከቻልን ብዙ ሃብት ለመቆጠብ ያስችላል ብለዋል።…

Read More

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል። በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና…

Read More

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጥቅምት 18 ቀን፣ 2018 ዓ.ም፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በመወያየት የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽን ያጸድቃል::

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

Read More