የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ መማር ማስተማር ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ::
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማሩን ስራ ለማስቀጠል በመንግስት፣ በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡ የኮቪድ-19 መከላከል መሥፈርቶችን በማሟላት ሁሉም ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር ለመጀመር ዝግጅታቸውን መጠናቀቃቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ ለዋልታ ቴሌቪዥን እንደገለጹት በድሬዳዋ አስተዳደር የትምህርት ስራውን ለማስጀመር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር…


