በግንዛቤ ማዳበሪያ መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን የኮሚሽኑ አባላት በተመረጡበት አካባቢ እንዴት ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው በቂ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ስራ ለመግባትና ያሉትን ክፍተቶች ለመዝጋት ስልጠናው ያግዛል ብለዋል።
በመድረኩ የቀረቡ 3 አጀንዳዎች የብልጽግና ፓርቲ ቁጥጥርና ኢኒስፔክሽን የውስጥ አሰራር እና የስራ አፈጻጸም ክትትል መመሪያ፣ በኮሚሽኑ እቅድ እና በሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ ዙሪያ በአስተዳደሩ ለሚገኙ የከተማ ቀበሌና የገጠር ክላስተር ኮሚሽን አካላት ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።
በመመሪያው ስለ መመሪያው ዓላማ፣ የኮሚሽኑ አሰራር መሰረታዊ መርሆዎችና እሴቶች፣ የኮሚሽኑ አወቃቀርና አሰራር ስርአት፣ የውሳኔ አሰጣጥና ተጠያቂነት፣ የዲሲፒሊን ጉድለት በሚፈፀሙ የኮሚሽኑ አመራሮችና የፓርቲው አባላት ላይ ስለሚኖር ቅጣት፣ የአባላት መብት አጠባበቅ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥነ-ሥርዓት፣ የፋይናንስ፣ የንብረት፣ የሰነድ አያያዝና አጠቃቀም ሥርዓት፣ የሱፐርቪዥን ስራዎች ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች እና ተዛማች ጉዳዮች በኮሚሽኑ አባል አቶ ቴዎድሮስ ባቹሬ ቀርቧል።
በመጨረሻም በቀጣይ የኮሚሽኑ እቅድና የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ በማቅረብ በሰነዶቹ ሰፊ ውይይት በማድረግና በማጠቃለያው በትኩረት መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች በመግባባት መድረኩ ተጠናቀቀ።
ምንጭ ፡- ብልፅግና ፓርቲ የፌስ ቡክ ገፅ


