በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ሴክተር ተቋማትና ቀበሌዎች የ2013 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡
ሪፖርት ግምገማው ለተከታታይ አምስት ቀናት በማካሄድ ጥር 8/ 2013 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
የሪፖርት ግምገማ የንግድ ኢንዱስትሪና ኢኒቨስትመንት ቢሮ በማቅረብ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም በዛሬ እለት በሚደረገው የሪፖርት ግምገማ ግብር ውሃና ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ፣ ኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲሁም መሬት ልማትና ማኔጅመንት በቅደም ተከተል የሚያቀርቡ ይሆናል ፡፡


