የጥምቀት በአል በድሬደዋ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርአት ተከብሯል፡፡

    በድሬዳዋ አስተዳደር የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ሲሆን ታቦታት ከጥምቀተ ባህሩ ተነስተው በካህና፣በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው የድሬዳዋ መገለጫ የሆነውን የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመቻቻል እሴት በሚያሳይ መልኩ እና ወደየ ደብራቸው ሀይማኖታዊ ስርአቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ ተመልሰው ገብተዋል ።